PDFሞባይል ጥገና መሰረታዊ ትምህርት
Bereketab Blood
ETB 399FULBEK
Direct Marketplace
Accounts, products, payments, verification, and payouts.
Digital downloadProduct details
ኤሌክትሮኒክስ በዘመናችን የሕይወታችን ዋና አካል ሆኗል። ከሞባይል ስልክና ኮምፒውተር ጀምሮ እስከ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ቻርጀር፣ የኃይል አቅርቦትና ብዙ የቤት እና የስራ መሳሪያዎች ድረስ ኤሌክትሮኒክስ በየቦታው ይገኛል። እነዚህ መሳሪያዎች ሲበላሹ ችግሩን መለየትና በትክክል መጠገን የሚችል ባለሙያ እጅግ ያስፈልጋል።
ይህ “መሰረታዊ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና” መጽሐፍ ኤሌክትሮኒክስን ከመሰረቱ ጀምሮ በቀላልና በተግባራዊ መንገድ ለመማር የተዘጋጀ ነው። ጀማሪዎች የኤሌክትሮኒክስን መሰረታዊ ሕጎችና ኮምፖነንቶች እንዲረዱ፣ በMultimeter ትክክለኛ መለኪያ እንዲያደርጉ፣ የCircuit ችግሮችን እንዲመረምሩ እና የተበላሸ Components እንዲለዩ ያግዛል።
በመጽሐፉ ውስጥ Voltage፣ Current፣ Resistance፣ Ohm’s Law፣ Series እና Parallel Circuit፣ Resistor፣ Capacitor፣ Diode፣ LED፣ Transistor፣ MOSFET፣ Inductor፣ Transformer፣ IC እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ Components በመሰረታዊ ደረጃ ይብራራሉ።
ከዚህ በተጨማሪ Soldering እና Desoldering፣ Multimeter አጠቃቀም፣ Continuity እና Diode Test፣ Short Circuit መፈለግ፣ Fault Finding፣ Component Testing እና የRepair ሂደት በተግባር የሚረዱ መልኩ ተካትተዋል።
የዚህ መጽሐፍ ዓላማ አንባቢው ቃላትን ብቻ እንዲያውቅ ሳይሆን፣ “ችግሩ ምንድን ነው? የት ነው ያለው? እንዴት እመረምረዋለሁ? እንዴትስ እጠግነዋለሁ?” ብሎ በስርዓት ማሰብ የሚችል የጥገና እውቀት እንዲገነባ ማድረግ ነው።
“ኤሌክትሮኒክስን ማወቅ ከመለካት ይጀምራል፤ ጥገናን መማር ደግሞ ችግሩን በትክክል ከመለየት ይጀምራል።”
ይህ መጽሐፍ ለጀማሪዎች፣ ለኤሌክትሮኒክስ ተማሪዎች እና የጥገና ሙያን መማር ለሚፈልጉ ሁሉ የመጀመሪያ መመሪያ ይሆናል።
Verified buyers
No reviews yet. Only confirmed buyers can review this product.
More from this creator